Translate

Friday, November 30, 2012

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች - አስጨናቂ ድረስ /ክጉለሌ/

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ህዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም.
በወያኔ ዘመነ ስልጣን የተቃዋሚ ድርጅቶች ወይም የወያኔ አጃቢዎች ብዛት በመጀመሪያው ዓመታት ከሃምሳ በላይ የነበሩ ቢሆንም
በአሁኑ ወቅት ወደ አስራስምንት አካባቢ ዝቅ ማለታቸው ይታወቃል፤
ሀ) ለመሆኑ በሃያ አንድ ዓመታት የወያኔ አገዛዝ ዘመን ምን ስሩ? የኢትዮጵያን ህዝብ ጠቀሙት ወይስ ጎዱት?
ለ) የ1997ዓመተ ምህረት ምርጫ ውጤት የነሱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጥረት ወይስ አጋጣሚና ብሶት የወለደው?
ወያኔ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ አራያነት ያለው ስራ ለመስራት ሞከረ፤ በዚህም መስረት በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙትን ከሃምሳ
በላይ ብሄረስቦችን ብዙሃኑንም አናሳውንም አንድላይ በመጨፍለቅ የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በማለት ቀደም ሲል
ካደራጃቸው ብአዴንና ኦህዴድ ጋር በመጠርነፍ ኢህአዴግ ተሰኘ፦ ለማስገንጠል ያዘጋጃትን ኤርትራን ጨምሮ ወያኔ ባዘጋጀው
ዕቅድ መስረት በአዲሰ አበባ አፍሪካ አዳራሽ ለሚደረገው ስብስባ ላይ ለመገኘት ድርጅታችሁን አስመዝግቡ የሚል ድንገተኛ ጥሪ
አስተላለፈ፤ አጋጣሚውን ለመጠቀም የፈለጉ ግለስቦች ያለምንም ቅድመ ዝግጅት፤ የህዝቡን ፍላጎትና ይሁንታ ሳያገኙ
የብሄረስባችን ተወካዮች ነን በማለት፤ የተወስኑ ምሁራንን፤ ቦዘኔዎችንና አጋጣሚ ተጠቃሚዎችን(opportunists)፤ በሙሉ በወያኔ
ስልቻ ውስጥ ዘለው ጥልቅ ያሉትን በሙሉ ይዞ አለምን ጉድ ያስኘ ስብስባ አደረገ፦ በግዜ ሂደት ወያኔ አይጠቅሙኝም ያላቸውን
ከስልቻው እያወጣ ወረወራቸው፤በአካዳሚክስ ዕውቀታቸውና ልምድ ለዘለቄታው ጉዞ ድብቅ ፍላጎቴን ለማራመድ ይረዱኛል
ያላቸውን ደግሞ በጥንቃቄ መርጦ በመያዝ፤ ተቃዋሚነታቸውን ተቀብሎ ፅ/ቤት በመስጠት እንዳስፈላጊነቱ መንቀሳቀሻ በጀት
በመመደብ ተደራጁ ብሎ መርቆ ለቀቃቸው፦ ዓለምም ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ መስፈኑን አረጋገጠ፤ ኢትዮጵያ የምትባል አገር
እስከወዲያኛው የመበታተንና ከአለም ካርታ የማጥፋት ምዕራፉ ተከፈተ፦
መለስም በድንገት ተስወረ ተቃዋሚዎችም የአጀብ ጉዞአቸውን ቀጥለዋል፤ይኸው ሃያ አንድ ዓመት አለፋቸው፦ቀላል ዘመን ነው
ትላላችሁ? እንደታደሉት እነደነ ጃፓን ቢሆንማ ኖሮ እስካሁን ሁሉም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ይዳረሳቸው ነበር፦ መለስ
እንኩዋን ስልጣን ስልችቶት መተካካት የሚባል ፕሮግራም ሊጀምር እንደ ነበር ደጋግሞ ገልፆልናል ባይታመንም፦ በዚህ በወያኔ
ዘመን የተፈጠሩ ልጆች እኮ ዩኒቨርሲቲ እየጨረሱ በስራ ላይ እየተስማሩ ነው፦ ተቃዋሚ ተብየዎች ይኸን የአጎብዳጅነት ተቃውሞ
በዉድ አገራችን ኢትዮጵያ ለተተኪው ትውልድ ማስተማራችውም ታሪክ ይቅር የማይለው ትልቁ አሳዛኝ ክስተት ነው፤
በኢትዮጵያ ምግባረ ብልሹነት እንዲስፋፋ ዋናው የወያኔ አጀንዳ መሆኑን አሁን ድረስ ተቃዋሚዎች አለመረዳታቸውም ሌላው
አስገራሚ ጉዳይ ነው፤ ረጅም ዘመን በማንቀላፋታቸውና አልቻልኩም መረረኝ ማለት ባለመቻላቸው የሃገራችን ችግር ዉስብስብና
አደገኛ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ሆኗል፤ ከወያኔስ በምን ይለያሉ፤ ከተጠያቂነትስ እንዴት ያመልጣሉ፦ ማንኛዉም ዜጋ በሃገር ጉዳይ
ያገባኛል ብሎ የህዝብ ይሁንታን ካገኘ በሁዋላ ቸልተኝነት ማሳየት አይቻልም፤ ሃያ አንድ ዓመት ሙሉ ተቃዋሚ ነኝ በሚል ስም
ህዝብ የራሱን አማራጭ እንኩዋን እንዳይወስድ በማዘናጋት አገር የመበታተን አደጋ ላይ እስክትደርስ ድረስ ቁጭ ብለው
በማየታቸው ላደረሱት በደል ከፍርድ ማምለጥ አይቻላቸውም፦ ረጀም ዘመን በዋዝ ፈዛዛ የመለስና የወያኔ አጃቢ በመሆን
በማሳለፋችው፤ ችግሩ ስፍቶ ከቁጥጥር ውጭ በመሄዱና፤ ወጣቶች ሌላ አማራጭ እንዳይፈልጉ በማድረግ የወያኔ መሳሪያ ሆነዋል፤
ወጣቱ የስራ አማራጭ በማጣቱ በመከላከያ ስራዊትና በወያኔ የስለላ መዋቅር ውስጥ በመግባት በወገን ላይ ኢስብአዊ ተግባር
ለመፈፀም መገደዳቸው ሌላው አሳዛኝ ክስተት ነው፦ መለስና ኢሳያስ በፈጠሩት ስራዊት ቅነሳ ጦርነት ውስጥ ለደረሰው ዕልቂት
የጠየቀ የለም፤ መለስ የውጭ ምንዛሪ በቸገረው ቁጥር ሶማሊያ እያስገባ ለሚይስጨርሰው ወጣት ጠያቂ የለም፤ መለስ ዜናዊ ገና
ከመስረቱ ለተቃዋሚውች እቅጩን ነግሯቸዋል፤ የልጅነት ዘመኔን ጫካ ለጫካ ተንከራትቼ ያገኘሁትን ስልጣን እዚህ ቁጭ ብላችሁ
ለማግኘት አታስቡ፤ እንዲደነግጡም እኔ በሄድኩበት መንገድ መቀጠል የሚፈልግ ካለ መንገዱን ጨርቅ ያርግለት ብሎ ሌላ
አማራጭ ወይም የትጥቅ ትግል እንዳያስቡ ለማስፈራራት ሞከረ፦ ከዚህ በሁዋላ ችግር ፈጣሪ አለመሆናቸውን አረጋገጠ፤
ወዲያዉኑ አርባ ሁለት ያገሪቱ ምርጥ ምሁራንን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያለ ምንም ምክንያት በማንአለብኝነት ሲያባርር ሰላማዊ
የተቃውሞ ትግል ማካሄድ ይቅርና የሃገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል አመላካች ሆነ፦ መልዕክቱ ግልፅ ነበር
ከእንግዲህ ትምህርት በኢትዮጵያ በቃ፤፤ ያልተማረ ያልተመራመረን ህዝብ መግዛት በሁሉም መልኩ ቀላል ስለሚሆን፤ አገርን
የመበታተን የመጀመሪያው ምዕራፍና የመለስም ትልቁ ስኬት ሆነ፤ ሃያ አንድ ዓመት አገር አጥፍቶ በብሄርና ቑንቑ ከፋፍሎ
ለወደፊትም ኢትዮጵያ በፍጥነት ወደ ነበረችበት እንዳትመለስ አድርጎ ሄደ፦ ይህ ሁሉ ሲሆን ተቃዋሚዎች አብረዉት አሉ፦
ሲፈልግ በየተራ እየጠራ ስልጣን ወይም ገንዘብ እያሳየ አጉምጅ ይላቸዋል፤ ሁሉም የሚንጠባጠብ ስልጣን አገኛለሁ በሚል ምኞት
የወጣትነት ዘመናቸውን ያለጠንካራ የተቃውሞ ትግል በዋዛ ፈዛዛ ጨረሱ፦
በዚህ መጥፎ ዘመን ለተፈጠሩት ልጆቻችን ቶሎ ማዳኛ መንገድ እስካልፈለግንላቸው ግዜ ድረስ ለወያኔ እጅ ቢስጡ ምን
ይደንቀናል፤ በተቃዋሚዎች ድክመት ወያኔ ያሻውን እያደረገ ይገኛል፤ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ በቅድሚያ የወያኔ አባል እንዲሆኑና ቅፅ
እንዲሞሉ ሲጠየቁ ተቃዋሚዎች ደርሰው ማስጣል ካልቻሉ፤ ከዩኒቨርሲቲ ጨርስው ሲመረቁ ኮብልስቶን እንዲያመርቱ ድንጋይ2
ፈለጣ ተሰማሩ እያሉ የወያኔ ባለስልጣናት ሲቀልዱ ኡኡ ብለው ህዝቡን አደባባይ ይዘው ካልወጡ፤ የኑሮ ዉድነት ስንጎ ይዞት
የሚላስ የሚቀመስ ቸግሮት ይህ ኩሩ ህዝብ አደባባይ ልመና ሲወጣ እሪ ያገር ያለህ ብለው አደባባይ ይዘውት መውጣት ካልቻሉ፤
በስንት መከራ አጠራቅሞ የስራትን ጎጆ በዶዘር ሲያፈራርሱበት ካልደረሱለት፤ የኑሮ ዉድነቱ አስቃይቷቸው አጠቃላይ የኢትዮጵያ
ህዝብ በሚያስብል ደረጃ በአገሩም ከአገሩ ውጪም ሲስደድ፤ በዚህ ሂደት ላይ ያስበው ቦታ ሳይደርስ ውቅያኖስ ውስጥ ሰመጡ፤
ኮንቴነር ውስጥ ታፍነው አለቁ ሲባል ምን ሲደረግ ካልተባለ፦ከስደት የከፋውም በአረብ ሃገራት በሴት ልጆቻችን ላይ
የሚፈፀመው ግፍ ካላስጮሃቸው፤ መድረሻ አጥቶ የወያኔ አሽከር ለመሆን ሲገደድ አማራጭ እንዲያገኝ ካላደረጉት፤ ወጣቱ የአገር
ፍቅር ስሜቱ ተሟጦ አልቆ ተስፋ ቆርጦ ራሱን ማጥፋት ደረጃ ላይ ሲደርስ እያዩ ዝም ካሉ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በጨለማ ውስጥ
ሲዳክር እንደ ሙሴ መብራት ሆነው ከመከራው ካላወጡት፤ ምኑንና ማንን ለመቃወም ነው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተብለው
የተጎለቱት፦ በጋዜጣ ላይ ቀረርቶና ፉከራ ለማስማት ከሆነማ በተሻለ መልኩ የተቃዋሚዎቹን ድርሻ ጋዜጠኞች እየተወጡት ነው፦
ተቃዋሚዎች የትጥቅ ትግልን ሊፈሩት ባልተገባ ነበር ካልሆነም የሚታገሉትን ለመርዳት መጣር አስተዋይነት ነበር፤ለመሆኑ በ97
ምርጫ መለስ አዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን በክልሎችም ኢህአዴግ ተሽንፈናልና ስልጣን ተረከቡን ቢላቸው ኖሮ ምን ያደርጉ ነበር?
እዉን ቤተ መንግስት ገብተው ሚኒስትሮችቸውን ሾመው የፌዴራልና የክልል አስተዳደራዊ መዋቅሮችን ዘርግተው ከሁሉም በላይ
የመከላከያንና የደህንንቱን ስራዊት ተቆጣጥረው ስላማዊ ሽግግር ተደርጎ አገር እንመራለን ብለው ከልብ አስበው ይኾን፦ይኽን
የሚያስቡ ሳይሆን የሚያልሙ እንኩዋን ካሉ ቂሎች መሆን አለባቸው፦
በአንድ ወቅት በፓርላማ ውስጥ አሳፋሪ ትዕይንት አይተናል፤ በጀት አመዳደቡ ትክክል አይደለም በሚል ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ
ለመለስ አቤቱታ ሲያቀርቡ ለኢዴፓ ከፍተኛ በጀት ሲመደብ ለኛ ድርጅት ግን አነስተኛ ነው በሚል፤ እንዴት ነው ወያኔ
በሚመድብላቸው በጀት እየኖሩ የወያኔ ተቃዋሚ ሆነው መቀጠል የሚችሉት፦ ለዚህም ነው መለስ እነዚህን ታማኝ ተቃዋሚዎችን
የሚፈልጋቸው፤ድፍን አስራ ስምንት ዓመታት ሙሉ መለስ ፈቅዶ ባስገባቸው ፓርላማ ውስጥ ሲሰድባቸው ሲሳለቅባቸው ሲፈልግ
ሲያስራቸው ሲያሻው መፈታት ከፈለጋችሁ የይቅርታ ደብዳቤ ፅፋችሁ ጠይቁኝ እያለ ሲቀልድባቸው ሲፈለግ ስደት እንዲሄዱ
ሁኔታዎችን አመቻችቶ ሲሽኛቸው፤በአጠቃላይ የፈለገውን ሲያደርጋቸው ኖሮ ተገላገሉት፦ በፓላማም ውስጥ የዉጭ ዲፕሎማቶች
በሚጋበዙበት ወቅት መለስንና ኢህአዴግን በማብጠልጠል ነፃነትና ዴሞክራሲ ያለ ለማስመስል በሚደረገው ድራማ ተዋናይ ሆነው
እንዲታዩና ዲፕሎማቶቹ የተሳሳተ ግንዛቤ ይዘው እንዲሄዱ ሲደረግ ተኑሯል፦አሁን ደግሞ የራሳቸውን ልጅ ሃይለማሪያምን
ተክሎላቸው ሄደ፦ሂደቱ ይቀጥላል የሚለወጥ ነገር የለም ብሏቸዋል፦ ተቃዋሚነታቸውን ቀጥለዋል፤ ዓለምም ልፍስፍሶች ሆነው
ነው እንጂ ጠንካራ ቢሆኑ ኖሮ መንግስት ከዚህ በላይ ምን ያድርግ በማለት እየተሳለቀባቸው ነው፦ ተቃዋሚ ስላለም ዲሞክራሲ
ስፍኗል በሚል የበለፀጉ አገራት እርዳታና ድጋፍ ይቀጥላል፦የኢትዮጵያ ህዝብ ስቆቃም ይቀጥላል፦ወያኔም የሚፈልገው ይኽንኑ
ነው፦
ተቃዋሚዎች እባክችሁን ከመጠየቅ ባታመልጡም የህዝቡን መከራ አታብዙት ወያኔን ከመለመን እናንተን መለመን ስለሚቀል
ይብቃቸሁ፤ፓርቲዎቻችሁን አፍርሱ፤ድርጅቶቻችሁን ዝጉ፤ የሃያላን መንግስታት አመለካከት አታዛቡ፤ የናንተ መኖር የወያኔ
ዓመታዊ በጀት እንኩዋን የሚታቀደው ግማሹ ከውጭ በሚገኝ ዕርዳታ መሆኑን ሃያ አንድ ዓመታት ሙሉ የተመለከትነው ነው፦
ወያኔ እርቃኑን የሚቀረውና ዕድሜውም የሚያጥረው እናንተ ሳትኖሩ ነው፦ የትጥቅ ትግል የሚያደርጉትን ባትደግፉም አትተቹ፤
ነገ መጠያየቅ ስለሚኖር፤ በአሁኑ ወቅት የሰራዊቱ አባላት በርካታወቹ ትግሉን የተቀላቀሉ ሲሆን በአጭር ግዜ ዉስጥ አብዛኛው
ስርአቱን ለመክዳት በዝግጅት ላይ መሆኑ ተረጋገጧል፦ ይቀጥላል
አስጨናቂ ድረስ /ክጉለሌ/
baschenaki44@gmail.com

No comments:

Post a Comment